Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Bible
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን::ይህ መጽሐፍ ቅዱስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ሥርዓትና ደንብ ጠብቆ የተዘጋጀ ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍ ነው:: መጽሐፉ ለሃይማኖት አባቶች ለሰባክያነ ወንጌልና ለመምህራን ለመንፈሳዊ ተልዕኮ በሚሰማሩበት ወቅት መጽሐፍ ቅዱስ በእጃቸው መያዝ ሳይኖርባቸው በቀላሉ ቃለ እግዚአብሔርን ለማስተማር ጉልህ አስተዋጽኦ ይኖረዋል:: ምዕመናንም የግዕዙንና የአማርኛውን ትርጉም ምሥጢሩ ሳይዛባ በስልካቸው እንዲጠቀሙ ይረዳል:: የመጽሐፉ ልዩ ባሕርያት † ሰማንያ አንድ (81) መጻሕፍትን ያካተተ ነው† ሙሉ ብሉይና ሐዲስ ኪዳን በኢትዮጵያ ጥንታዊ ቋንቋ በግዕዝና በአማርኛ የተዘጋጀ ነው † የአማርኛው ትርጉም በጥንታዊው የአባቶቻችን አጻጻፍና አገላለጽ ሃይማኖታዊ ለዛውን ሳይለቅ የተጻፈ ነው † የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የምትጠቀምባቸውን የብሉይ ኪዳን የቀኖና መጻሕፍት ያካተተ ነው † ፊደሉና አጻጻፉ በግእዝና በአማርኛ መዛግብተ ቃላት መሠረት ታርሞ የተዘጋጀ ነው።† የፊደሎችን መጠን በቀላሉ ማስተካከያ መንገድ አለው ማሳሰቢያ: መጽሐፍ ቅዱሱን በየጊዜው ስለምናዘምነውና ያልተሟሉ የመጻሕፍት ክፍሎችን ስለምናሟላቸው የFacebook ገጻችንን Like በማድረግ አዳዲስ ነገሮችን ያግኙ:: http://www.facebook.com/getahun.amare1 This Ethiopian Geez Amharic Orthodox Bible android app is the only complete 81 books from Old, New Testament books and Deuterocanon/Apocrypha books. It is the best Android Bible that contains both Geez and Amharic Orthodox bible translationsIf you like this App Rate us and give us a review.